• አዲስ ጽሁፍ አንድ
  • አዲስ ጽሁፍ ሁለት
  • አዲስ ጽሁፍ ስስት
  • አዲስ ጽሁፍ አራት
  • ጠቃሚ ገጽ አንድ
  • ጠቃሚ ገጽ ሁለት
  • ጠቃሚ ገጽ ሶስት

የኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የክርሰትና እምነት ፈለግ በመከተል ጸንታ ትቆማለች፡፡

I. ቅዱሳት መጻሕፍት

የሁለቱንም ብሉይና ሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት የያዘ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ከእግዚአብሔር አፍ እንደወጣ እንደማይለወጥ በእምነታችንና በነገር ሁሉ ወሳኝና ፍጹም ሥልጣን እንዳለው ቃል ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱን በሙላት የገለጠበትና በመንፈሱም መሪነት እንደተጻፈ እናምናለን፡፡

እግዚአብሔር በመጻሐፍ ቅዱስ ካለው የእውነት ቃል ጋር የማይስማማ ወይም የሚቃረን ሌላ አዲስ መገለጥን አይሰጥም፡፡

II. እግዚአብሔር

በሦስት አካላት አብ ፣ወልድና ፣መንፈስ ቅዱስ /ሥላሴ/ ሆኖ ከዘላለም እስከዘላለም ይኖራል፡፡ሦስቱም በመለኮት ፣በባህርዩና፣ በሥልጣን አንድ ስለሆነ አንድ አምላክ ብለን እናምናለን፡፡

III. እግዚአብሔር አብ

ዘላለማዊ ሰማይንና ምድርን የሚታይና የማይታዩትን የፈጠረ የህግ ሁሉ ምንጭ ሁሉን የሚገዛ ሁሉንም በሁሉ የሆነ አምላክ እናምናለን፡፡

IV. እግዚአብሔር ወልድ

ጌታ እየሱስ ክርስቶሰ ዘላለማዊ የአብ አንድያ ልጅ የሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል መሪያም የተወለደ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ የሆነ ሀጢያተ በሌለበት ህይወቱ በታምራቶቹና በትምህርቱ አብን በሙላት የገለፀ ያለምንም በደል ለሀጢያታችን ቤዛ ሆኖ በመስቀል የሞተ የተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በሥጋ የተነሰ ለሰዎች የታየ ወደሰማይ ያረገ አሁንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ ስለኛ የሚማልድ መንግስቱን በፅድቅና በሰላም ይመሰርት ዘንድ በታላቅ ሀይልና በክብር ዳግመኛ የሚመጣ መሆኑን እናምናለን፡፡

V. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

አፅናኝ ወደእውነት ሁሉ የሚመራ ለነብያትና ለሓዋርያት ቃሉን የገለፀ ዛሬም ባማኞች ልብ አድሮ ኃይልን ላገልግሎትና ቤተክርስቲያንን ለማነፅ የፀጋ ስጦታዎችን የሚሰጥ አለምን ስለሀጢያት ስለፅድቅና ስለፍርድ የሚወቅስ አምላክ መሆኑን እናምናለን፡፡

VI. ሰው

አስቀድሞ በእግዚአብሔር አርእያና አምሳል የተፈጠረ፡፡ በሀጢያትም ወደቀ ከዚያም የተነሳ በመንፈስና በስጋ ሟች ሆነ የህም መንፈሳዊ ሞትና ስጋዊ ድካም ሰው ሆኖ ከተገለፀው ከእየሱስ ክርስቶሰ በስተቀር በሰው ዘር ሁሉ የሚተላለፍ ተፈጥሮአዊ ባህርይ ሆነ ሰው ጌታ እየሱስ ክርስቶሰ በፈፀመው ስራ በፀጋ ብቻ ይድናል፡፡

VII. ደህንነት

ክርስቶስ እየሱስ ለሰዎች ሁሉ እራሱን መስዋዕተ አድርጎ በመስቀል ከከፈለው ዋጋ ደህንነት ለሰው ልጆች ሁሉ ሆኖል፡፡

ከጥንት ከአዳም የተወረሰና የአለምን ሀጢያት ሁሉ የሚያነፃ እውነተኛ አዳኝና ቤዛ ይህ ብቻ ነው፡፡ የተፈፀመውንም የደህንነት ስራ በትንሳኤው ተረጋግጡአል፡፡

ንስሃ ገብተው በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ ይወለዳሉ፡፡የዘላለምንም ህይወት ያገኛሉ፡፡

VIII. በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አመኝ እራሱን ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ የሚያስገዛበት በዚያም ክርስቶስን የበለጠ እንዲያውቅ በመንፈሳዊ ህይወቱ እንዲያድግና መልካም ምስክር እንዲሆን የሚየስችለው ኃይልን የሚቀበልበት ልምምድ ነው፡፡ እንደጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ቃልም አማኞች ሁሉ ይህንን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከልባቸው እንዲሹ ይገባል፡፡

IX. የፀጋ ሰተጦታዎች

አማኞች ቤተክርስቲያንን ለማነፅና ለማንፃት የእግዚአብሔር ህልውና በቤተክርስቲያን እንዲገለፅና አገልግሎታቸውን በሚገባ እንዲፈፅሙ የሚያሰችላቸው ከእግዚአብሔር የሚሰጣቸው መለኮታዊ ኃይልና ልዩ ችሎታዎች ናቸው፡፡

X. ፈውስ

በክርስቶስ እየሱስ በኩል የሀጢያት ስርየትና ፈውስ ለአማኞች ሁሉ ተሰጥቷል፡፡ ስለዚህም ለታመሙ ፀሎት በፀጋ ስጦታዎችም ፈውስ ቤተክርስቲያን ታበረታታለች፡፡

XI. ቤተክርስቲያን

ክርስቶስን በሚያምኑ መሀበረ ምእመናን አንድነት የተመሰረተች አለማቀፍ አካልነት ያላት የክርስቶስ ሙሽራ ናት የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አማኞች በአንድነት እግዚአብሔርን የሚያመልኩባት ቅዱስ ሚስጥራተን የሚያካሂዱባት በእምነት ቃል እንደታዘዘም ወንጌልን ለአለም ሁሉ ለማዳረስ ተልእኮ የሚፈፅሙባት በእግዚአብሔር የተመሰረተች አካል ነች፡፡

XII. ቅዱስ ሚስጥራት

ቤተክርስቲያን ከዚህ በታች የተገለፁትን ቅዱስ ሚስጥራተ በሚገባ እንዲጠበቁ ሃላፊነት አለባት

ሀ. ቅዱስ ቁርባን

የጌታን መከራና ስቃይ ለማሰብና ሞቱንና ትንሳኤዉን ለመናገር የሚደረግ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናን ሁሉ ቅዱስ ቁርባንን ጌታ እስኪመጣ ድረስ ይካፈላሉ፡፡

ለ. የውሃ ጥምቀት

አማኞች በሞት መቃብርና በትንሳኤ ከክርስቶስ ጋር እንደመሆናቸው የሚያሳዩበት በአብ በወልድና በመንፈስቅዱስ ስም በውሃውስጥ በመንከር የሚፈፅሙት ስርአት ነው፡፡

XIII. ቅዱስ ጋብቻ

አማኝ ወንድምና እህት በጋብቻ አንድ እንዲሆኑ በቅድስና የተመሰረተ ትዳር እንዲመሰርቱ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ጋብቻ ስነስርዓትን ታካሂዳለች፡፡

XIV. ትንሳኤ ሙታን

ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በስጋ እንደተነሳ ሁሉ ፃድቃንና ኃጥአንም ከሙታን ይነሳሉ ፡፡ ፃድቃን በመንግስተሰማያት ዘላለማዊውን የእግዚአብሔርን ክብር ይወርሳሉ ኃጥአንም ይፈረድባቸዋል፡፡ ወደዘላለም ቅጣትም ይጣላሉ፡፡ ይህ ሁለተኛው ሞተ ነው፡፡

XV. መነጠቅ

የቅዱሳን ሁሉ ተስፋ በሚሆን የክርስቶስ ምፅአት አናምናለን፡፡ በክርስቶስ ሆነው የሞቱት አስቀድመው ይነሳሉ፡፡ ህያው ሆነው የሚቀሩትም ይለወጣሉ፡፡ሁሉም በአንድነት ጌታን በአየር ለመቀበል ይነጠቃሉ፡፡ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር ይሆናሉ፡፡

XVI. የክርስቶስ ዳግም ምፅአት

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መንግስቱን ይመሰርት ዘንድ ዳግመኛ እንደሚመጣ እናምናለን፡፡ ሙታንን ያስነሳል በሰው ልጆች ሁሉ ይፈርዳል፡፡ አመፀኞች ከእግዚአብሔር ህልውና ለዘላለም ይለያሉ፡፡ ፃድቃን ግን ከእርሱ ጋር ለዘላለም ይኖራሉ፡፡

XVII. መላዕክት

በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ኃያላንና ረቂቃን ፍጥረቶች የእግዚአብሔርን አላማ የሚፈፅሙ ቅዱሳንን ከክፉ የሚጠብቁ ሁልቆ መሳፍርት የሌላቸው የሰማይ ሰራዊትና የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፡፡

XVIII. ሰይጣን

ሰይጣን የሀጢያት ሁሉ ጀማሪ በእግዚአብሔር ላይ ያመጹትን ተከታዮቹን ይዞ በትዕቢት የወደቀ ፍጡር ነው፡፡ ከእርሱ ጋር የወደቁትንም አጋንንትና እርኩሳን መናፍስት ሆነው የእግዚአብሔርን አላማ በመቃወም በትጋት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ አማኝ ክርስቲያን ከእርኩሳን መናፍስት ተፅዕኖና ጭቆና ፍፁም ነፃነትን በአጋንንትም ላይ ፍፁም ድልን በክርስቶስ ተቀዳጅቷል፡፡ ባለማቋረጥም እየተቃወመ ያርቃቸዋል፡፡

XIX. መንግስተ ሰማያት

ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም የሚኖሩባት ቅድስተ ሰማያዊት ስፍራ ነች፡፡

XX. የእሳት በህር (ሁለተኛ ሞት)

ዳቢሎስና ተከታዮቹ ለዘላለም በስቃይ ሊኖሩባት የተዘጋጀች የቅጣት ስፍራ ነች፡፡

XXI. የመጨረሻው ፍርድ

የመጨረሻው ፍርድ ከታላቁ ነጭ ዙፋን ለሁሉ እንደስራው ይሆናል፡፡ ማንም በህይወት መፅሀፍ ያልተገኘ እርሱ ለዘላለም ቅጣት ወደእሳት ባህር ይጣላል፡፡ በህይወት መፅሀፍ የተገኘ በመንግስተ ሰማያት የዘላለም ህይወት ይወርሳል፡፡


  • ጥቅስ መፈለጊያ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መመሪያ

© Copyright 2011 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ኦቶዋ፤ ካናዳ

  • ራዕይ
  • |
  • የእምነት አንቀጽ
  • |
  • ተልዕኮ
  • የሀ መዘምራን
  • |
  • የረድኤት አገልግሎት